በፍርድ ባለመብት ዳይናሚከ ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኢማ እና በፍርድ ባለእዳ አቶ ሽመልስ ከበደ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 96068 በቀን 11/04/2016ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.99200 በቀን 14/05/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በኮ/ቀ/ከ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 817 የሆነ ቤት የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000090607345 የይዞታ ስፋት 15
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት ዳይናሚከ ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኢማ እና በፍርድ ባለእዳ አቶ ሽመልስ ከበደ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 96068 በቀን 11/04/2016ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.99200 በቀን 14/05/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በኮ/ቀ/ከ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 817 የሆነ ቤት የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000090607345 የይዞታ ስፋት 150ካ.ሜ የሆነ ይዞታ አቶ ሽመልስ ከበደ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር6,545,700( ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ብር )ሆኖ የትራዛከሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 7 ቀን 2018ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከı/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በı5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወርግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
