Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline11 Aug 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening date2026-08-11 14:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

የፍ/ባለመበት ወ/ሪት እየሩሳሌም ንጉሴ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ከበቡሽ መለሰ (10 ሰዎች) መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/190914 በ9/11/2016 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/202824 በየካቲት 25 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ//ከተማ ወረዳ 05 የሚገኝ የቤት ቁጥር 828/ሀ በመለያ ቁጥር AA00080502795/2 - ስፋቱ 241.255 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 8,895,714.35 (ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ሰባት መቶ አስራ አራት ብር 35/100 ብር) ሆኖ የትራዛሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ምንም ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 202824 በቀን ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 2,223,928.58 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ስምንት ከ58/100) ሆኖ የትራዛሽን ታስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ ሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O ሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችመሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

Save Tender