ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ:የተለያዩ የፎርድ መለዋወጫ ዕቃዎች
የጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተዘረዘሩት የተለያዩ የፎርድ መለዋወጫ ዕቃዎች አጠቃላይ መመሪያዎ እና ግዴታዎች፦
1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ደንበኞች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 20 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የሚጫረቱበትንዋጋ በሰም በታሸገኤንቬሎፕ በማቅረብ በጨረታ ሰነድ ቅጽ ላይ በመሙላትና ለጨረታ ማስከበሪያም ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ በማስያዝ በድርጅቱ የፎርድ መለዋወጫ ዕቃዎች ዲቪዥን ከፍል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
3. በዚህ የግዢ ጨረታ የሚቀርቡ ሰነዶች በሙሉ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ መጻፍ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ለመግዛት የወሰኑበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ለእያንዳንዱ መለዋወጫ ዕቃ መለያ ቁጥር በተናጥል መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚፈልጉትን የሚለዋወጫ አይነት በመለየት በጥቅል ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ::
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመከፈል ከድርጅቱ የፎርድ መለዋወጫ ዕቃዎች ዲቪዥን ገንዘብ ተቀባዮች ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ዘግይተው የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
8. ጨረታው የጨረታ ሰነዱን ማስገቢያ ጊዜ ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የሰራተኞች ክበብ ውስጥ ይከፈታል፡፡
9. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለጸ ቀን አንስቶ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ ዕሴት ታክስን ጨምሮ ክፍያ መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡
10. በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ያሸነፉበትን ዕቃዎች የማያነሱ ከሆነ በእቃዎቹ ላይለሚደርሰው ጉዳት ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
11. የጨረታ ተሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቶ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011 442 1133 / 0944 06 80 06
ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ
