Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሔር ጉዳይ ችሎት
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline17 Aug 2026, 12:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening date2026-08-17 12:30:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍታብሔር ጉዳይ ችሎት የጋራ መኖሪያ ቤት/ኮንደሚኒየም መሸጥ ይፈልጋል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአፈጻጸም ፍርድ ባለመብት ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ ማህበር አዳማ ቅርንጫፍ እና በፍርድ ባለእዳ ቤዛ ተገኝ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ክርክር አስመልክቶ በአዳማ ከተማ ሀንጋቱ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውን የጋራ መኖሪያ ቤት /ኮንደሚኒየም/ የሆነ እና የባለቤትነት ማስረጃ የካርታ ቁጥር 001191/2003 በወርቁ ታደሰ ስም ተመዝግቦ ያለውን የጨረታ መነሻ ዋጋ የቤቱ ግምት 1,523,450 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ብር) የሚያወጣ ግልጽ በሆነ ጨረታ በቀን 11/12/2018 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡30 ቤቱ በሚገኝበት ቦታ መግዛት የሚፈልግ ግለሰብ (ተቋም) የጨረታ ኮሚቴ አወዳድሮ የሚሸጥ መሆኑን እየገለጽን መግዛት የሚፈልግ ቀርቦ መግዛት የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን።

ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ከ 9/11/2018 እስከ 9/12/2018 ለተከታታይ ቀናቶች ማስታወቂያው የሚለጠፍበት ቦታ፣ ኦሮሚያ ከለቻ ጋዜጣ፣አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ አዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ዳቤ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ፣ አዳማ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ተለጥፎ የሚቆይ ይሆናል።

መግዛት የሚፈልግ ግለሰብ ተቋም የ1,523,450 (አንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ብር) የመነሻ ግምቱን 25% ሲፒኦ በባንክ ገቢ ማድረጉን ማስረጃ ማቅረብ አለበት።

 

በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍታብሔር ጉዳይ ችሎት

Save Tender