Tender Detail

Tender Details


ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡  


የሐራጅ ማስታወቂያ

ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  ተ.ቁ የተበዳሪው ስም

 

 

የንብረት አስያዥ ስም ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት አበዳሪው ቅርንጫፍ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት የጨረታ መነሻ ዋጋ

 

የጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት እና ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ

 

ጨረታው የወጣው
  ከተማ፣ ክ/ከ/ ወረዳ/

ቀበሌ

የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር የቦታ ስፋት በካ.ሜ/ሄክ
1 አቶ ሰለሞን ጋዲሳ ደስታ ተበዳሪው የንግድ ቤት መቂ ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ መቂ ከተማ 01 ቀበሌ 476/01/M-01 1000 1,438,005.36 በ13/12/2017 ከ8:00-9:00 ኦሮሚያ ባንክ መቂ ቅርንጫፍ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ
  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ባለ ዕዳዎቹ እና ታዛቢዎች ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡
  3. የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
  4. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  5. በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል፡፡ ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  7. ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል፡፡
  8. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ፡፡
  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 እና +251923587384 ወይም +251984380868 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት፣ ወይም በ022-1181188ኦሮሚያ ባንክ መቂ ቅርንጫፍ፣ለተ.ቁ 2-3 በ 0114671158/663 ኦሮሚያ ባንክ ሀዊ ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
  10. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኦሮሚያ ባንክ

Save Tender