Tender Detail

Tender Details


የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት የሰራተኛ ክበብ አገልግሎት፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የህትመት አገልግሎት እና የትራንስፖርት መኪና አገልግሎት አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል


 ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመስሪያ ቤቱ ስም የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት የግዢ የስራ ሂደት

v የሰራተኛ ክበብ አገልግሎት ጨረታ

v የመስተንግዶ አገልግሎት ጨረታ

v የህትመት አገልግሎት ጨረታ

v የትራንስፖርት መኪና አገልግሎት ጨረታ

የአቃ/ቃ/ክ/ከ ወረዳ 4 አስተዳደር ለወረዳው ሰራተኞች የካፌ አገልግሎት፤ መስተንግዶ፣  የትራንስፖርት መኪና እና የህትመት ስራዎች የ2019 በጀት ዓመት ለአንድ ዓመት አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም በዚህ ስራ ላይ የተሰማራችው ወይም የንግድ ስራ መስካችው  የሚጋብዛችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እናሳዉቃለን።

የጨረታው መስፈርቶች

1.    በዘርፋ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው/ያላት

2.    የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ተከታታይ ቀናት ከ2:30-11፡30 ሰአት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ፅ/ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 10 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3.    ተገቢውን የመንግስት ግብር የከፈለና ክሊራንስ ያለው/ያላት

4.    ከትራንስፖርት መኪና ውጭ ያሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ህጋዊ ደረሰኝ ያለው/ያላት

5.    ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል ግብዓት ሙሉ በሙሉ በማቅረብ መስራት የሚችል

6.    የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በኦሪጅናል እና በኮፒ ማቅረብ የሚችል

7.    ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ያቀረቡት የማወዳደርያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሸያ ማድረግ አይችሉም

8.    የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ. ለሰራተኛ ካፌ 20,000.00 ( ሃያ ሺህ) ለትራንስፖርት መኪና አገልግሉት 10,000.00 (አስር ሺህ) ብር ለህትመት አገልግሎት 10,000.00 (አስር ሺህ) ብር ለመስተንግዶ አገልገሎት 5,000.00 (አምስት ሺህ) ብር ማቅረብ የሚችል/የምትችል

9.    ጨረታውንያሸነፈተጫራች የውጪ ማስከበሪያዋስትና በአገልግሎቱ የተያዘውንበጀት 10% ሲፒኦ አዘጋጅቶ ፣ቅረብ የሚችል/የምትችል

10.        ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ታዛቢዎች ባሉበት በወረዳ 04  ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 106 የሚከፈት ሲሆን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው  ቀን የሚከፈት ይሆናል ሆኖም የተጫራቾችአለማገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።

11.        የውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው ከቀረበው የዋጋ ዝርዝር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበና በጠቀላላ ድምር  ዝቅተኛ ቀረበ ይሆናል።

12.        ውድድሩን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ7 ተከታታይ የቅሬታ ቀን በኋላ በአካል ቀርቦ ውል መማሪ ማንታ አለበት።

13.        መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

14.        የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደርአዋጅ ቁጥር 17 /2002 እና የማር አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 2/2002 በዚህ የግዢ ሂደት ተፈፃሚ ይሆናሉ።

15.        በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ኢንተርኘራይዞች በድጋፍ ደብዳቤ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የመስራቤቱ አድራሻ አዲስ አበባ ከፍለ ከተማ -- አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 4 አስተዳደር ልዩ

ስሙ : ገላን ቁጥር 2 ት/ቤት አጠገብ

የመጫረቻ ቦታ፡- በወረዳ 4 ፋይናንስ ፅ/ቤት

ማሳሰቢያ ፦

ማንኛውም ስርዝ ድልዝ ያለውን ማስረጃ ከጨረታው ውጪ የሚያደርግ መሆኑን እንገልፃለን

ለተጨማሪ መረጃ - 09 55 37 36 36 (09 20 85 77 29) በመደወል ማግኘት ይቻላል::

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04

ፋይናንስ ፅ/ቤት

 

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender