Tender Detail

Tender Details


የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የሚገኝ በሴቶች ፎረም የሚተዳደረውን ካፍቴሪያ በግልጽ ጨረታ በማውጣት ማከራየት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የመወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጂቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


2 ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የሚገኝ በሴቶች ፎረም የሚተዳደረውን ካፍቴሪያ በግልጽ ጨረታ በማውጣት ማከራየት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የመወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጂቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

1.     የጨረታ ሰነዱ ዓላማ ብቁ እና ህጋዊ የሆኑ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በዘርፉ በቂ ልምድና ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ መጋበዝ ነው፡

2.    ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 አምስት መቶ /በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ ግዥ ከፍል በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

3.    ተጫራቾች የመጫረቻ ዋስትና በሆሰፒታሉ ስም ብር 50,000/ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክበተረጋገጠ ሰፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.    ጨረታው የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዥ ክፍል ውስጥ አየር ላይ ከዋለበት ተከታታይ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ስዓት ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 430 በይፋ ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

5.    መስሪያ ቤቱ የውሃ እና የመብራት ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፡፡

6.    ተጫራቹ ድርጅት የጨረታው መዝጊያ ከመድረሱ 2 ቀናት በፊት በማንኛውም የስራ ሰዓት የካፍቴሪያ ቦታውን መጎብኘት እና ግልጽ ያልሆኑ ነገሮችን በአካልም ሆነ በጽሁፍ ግልጽ እንዲሆንለት መጠየቅ ይችላል፡፡

7.    አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት አዋርድ ከተሰጠበት ቀን ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አገልግሎቱን መስጠት መጀመር ይኖርበታል፡፡

8.    ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ፋይናንሺያል ኦርጂናል እና ኮፒ ቴከኒካል ኦርጂናልና ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ፖስታ ግልጽ ሆኖ በሚታይ መልኩ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

9.    ሆስፒታሉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።

 

 

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

 

Save Tender