የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለህዳሴ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የጥበቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ΕΕΡ/GBP/NCB/02/2019
1. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለህዳሴ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የጥበቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ .. እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንከ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 114 መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የጥበቃ አገልግሎት ግዥ በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸዉን ዝርዝር በታዠገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር CEEP/GBP/NCB/02/2019 የሚል ምልክት በማድረግ 1 (አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 375,000.00 (ሶስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ) ለ90 (ዘጠና) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ከፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ይከፈታል፡፡
7. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 40 11 መደወል ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
