አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ በሦስተኛ ወገን የሚፈጸም የጥበቃ አገልግሎት ግዥ
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ግዥ የጨረታ ቁጥር 002/2019
አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ኢንዱስትሪያችን በሸገር ከተማ በገላን ከፍለ ከተማ ውስጥ ለሚገኘው ኢንዱስትሪ የጥበቃ አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
- የ2018/2019 በጀት ዓመት ሕጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የጊዜ ገደቡ ያላለፈበት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከሚመለከተው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (Tax Clearance)፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (VAT)፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ በአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (PPA Website supplier list) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጥበቃ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከፖሊስ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጥበቃ አገልግሎት የሰጠ እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ደብዳቤዎች የሚያቀርብ።
- በጥበቃ ጉድለት ለሚፈጠር አደጋ ዋስትና የሚወስድ (የሚሰጥ) ኢንሹራንስ ያለው፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 22 በመምጣት እንዲያስገቡ ተደርጎ ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ሆኖ በእለቱ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በአቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ ስም ሒሳብ ቁጥር 1000014630906 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ-አርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት 7፡00-11፡00 ሰዓት ኢንዱስትሪያችን ቅጥር ግቢ በመቅረብ ሰነዱን ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50.000.00 (አምሳ ሺ ብር) በCPO ወይም bank guarantee ወይም Cash ቢያንስ ለ88 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
- ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከኢ/አ ወደ ዱከም መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ሽክር ከተማ የቀድሞ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ HASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0981641979 /0912088636
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ
✨ messages.ai_summary
Akaki Basic Metals Industry seeks security service providers for a one-year contract via open tender. Bidders must hold valid licenses, tax clearance, TIN, VAT, and PPA registration, plus police and labor office permits, insurance, and performance references.
