Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
  • Address ኮተቤ ብረታ ብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-42-95
  • Websitehttps://www.eep.com.et/?lang=am
  • Deadline03 Aug 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-08-03 14:00:00
  • Categories Water Well And Pool Cleaning , Water Well Drilling

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለማሰራት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታቁትር ΕΕΡ/GBP/NCB/01/2019

 

1.     የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለማሰራት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡

3.     ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንከ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው /ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2 ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህዳሴ ህንጻ 2 ፎቅ ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 14 መውሰድ ይችላሉ፡፡

4.     ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/01/2019 የሚል ምልከት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) 90 (ዘጠና) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ከፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6.     ጨረታው ሐምሌ 27 ቀን 2018 . ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 27 ቀን 2018 . ከቀኑ 830 ህዳሴ ህንጻ 2 ፎቅ ጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ይከፈታል፡፡

7.     ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8.     ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 40 11 መደወል ይችላሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

Save Tender