ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ድርጅታችን የሚገኝበት ዋና መስሪያ ቤት የሆኑትን ማለትም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሚገኘውን የህንጻው የዋና ስራ አስፈጻሚ ክፍል እና የስብሰባ አዳራሽ የእድሳት ሥራ ለማከናወን ተፈልጓል፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Commercial Nomminees PLC
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/01/2018
በዚህም
ሎት1፡- የህንጻው የዋና ስራ አስፈጻሚ ክፍል እና የስብሰባ አዳራሽ የዲዛይን እና ማማከር ስራ
ማከናወን የሚችሉ የኢንቴሪዬር ዲዛይን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
