Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
  • Address , Phone: +251911984467
  • Website
  • Deadline06 Aug 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-08-06 10:30:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products

ኮርፖሬሽኑ የፕላስቲክ ከረጢት ግዥ የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር ... ማዕከል ገዥ /ብግጨ 01/2018/19

ኮርፖሬሽኑ የፕላስቲክ ከረጢት ግዥ የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የፕላስቲክ ከረጢት

1.     ተጫራቾች በዘርፉ 2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.     ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታ መክፈቻው ቀን በኋላ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህበመክፈል ከሐምሌ 20 ቀን 2018 . ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 230 – 630 እንዲሁም ከሰአት 730 - 100 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 230 -630 ድረስ ማመልከቻ በመያዝ ብሎክ 2 አንደኛ ፎቅ ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ (አድራሻው ከስር ተገልጿል፡፡)

4.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5.     ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብርበሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

6.     ተጫራቾች ቴክኒክ እና ፋይናንስ ሰነድ በግልጽ ከፍለው በተለያየ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7.     ጨረታው ሐምሌ 30 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

8.     ከዋና የመወዳደሪያ ሃሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት 1(አንድ)

9.     አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን ለአሸነፉበት የፕላቲክ ከረጢት ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈፅሙ ይሆናል።

10.ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ደብረዘይት መንገድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርጫፍ ፊት ለፊት

... 7858 ስልክ ቁጥር 011 4167345/011 4669336

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender