በፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር የ17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር የ17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1. ጀኔሬተር
2. የፕላስቲክ እና የብረት ወንበር፣ ጠረጴዛ
3. የለስላሳና የቢራ ሳጥን
4. የተለያዩ የቢሮ ወንበር እና ጠረጴዛ
5. የድንኳን ብረት እና ብላስቲክ ድንኳን ያገለገሉ
6. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
7. ቁርጥራጭ ብረታ ብረት እና ከረንቡላ ሌሎች የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣ የቫት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ።
2. ሠነድ ሊወስዱ ሲመጡ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
3. በተጨማሪም የጠቅላላ ዋጋ የጨረታውን 2% በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው በወጣበት በስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሣጥን ይዘጋና በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የ17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ይከፈታል። በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓትን አያስተጓጉልም።
5. ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. የጨረታው ሣጥን ከታሸገና ሠነዶቹ መከፈት ከተጀመረ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ የጨረታውን መመሪያ አለማክበር ከጨረታው ያሰርዛል።
7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት የቅድመ ክፍያ፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም፣ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በማስያዝ ውል መግባት አለበት።
8. ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ሥራ/ማህበር ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር 17/17 ህብረተሰብ ልማት ሻላ መናፈሻ ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ የማዕከሉ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቀርበው ሠነዱን መግዛት ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ፡-
011 618 4076/ 011 618 7529 / 011 618 6504
ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር
