የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በምን/ሸ/ወ/አሞራቤት ቀበሌ የቀድሞው የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ሲጠቀምበት የነበረውን የባቡር ሃዲድ ሰብስቦ እንዳከማቸ ይታወቃል። ስለሆነም በአሞራቤት ቀበሌ መልካጅሎ እና ሃሩ አርባ ጎጥ ተከማችቶ ያለውን የሃዲድ ብረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019
የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በምን/ሸ/ወ/አሞራቤት ቀበሌ የቀድሞው የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ሲጠቀምበት የነበረውን የባቡር ሃዲድ ሰብስቦ እንዳከማቸ ይታወቃል። ስለሆነም በአሞራቤት ቀበሌ መልካጅሎ እና ሃሩ አርባ ጎጥ ተከማችቶ ያለውን የሃዲድ ብረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ቲን ነምበር፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሠነድ ከምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ገንዘብና ጽ/ቤት በ1000/አንድ ሺህ ብር/ ብቻ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታው ሠነድ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 የሚከፈት መሆኑን አውቀው የጨረታ ሠነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ። ሌሎች መስፈርቶችን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 022 223 0293/ 022 223 0017 በመደወል ይጠይቁ።
በሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
