የምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት በ2019 ዓ/ም ለታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውሉ ጥሬ ሰብሎችና የተለያዩ ማጣፈጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት በ2019 ዓ/ም ለታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውሉ ጥሬ ሰብሎችና የተለያዩ ማጣፈጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሱትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሱ እና በተወዳዳሪዎች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. ጥራት ያላቸውን የተጠየቁ ጥሬሰብሎች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው;
2. የተለያዩ ማጣፈጫዎችን እና የዳቦ ዱቄት ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
3. ለምግብ ማብሰያ የሚሆን ግንድላ /ማገዶ እንጨት ማቅረብ የሚችል፤
4. ተወዳዳሪዎች የተጠየቁትን ናሙና ሙሉ በሙሉ ማቅረብ አለባቸው፤
5. የ2018 ዓ/ም ግብር አጠናቅቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታከስ ከፋይነት (TIN) (TIN)
6. ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) 50.000.00 ብር ከኦርጅናል ማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር (100) በመከፈል የግዥ ክፍል ከምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ፤
8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዓይነቶች እንደዚሁም የድርጅቱን ስም በሚያቀርቡት ፖስታ ላይበኦሪጅናሉና በኮፒው ላይ በግልጽ በመጻፍ በድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተወዳዳሪዎች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
12. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ገዥው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር -0577710193 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
14. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት
