የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት እየተሰራ ለሚገኘው ለቶነጫሌ የመንገድ ስራ ፕሮጀከት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በዝርዝር የተገለፀውን ኮንከሪት ፓይፕ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት እየተሰራ ለሚገኘው ለቶነጫሌ የመንገድ ስራ ፕሮጀከት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በዝርዝር የተገለፀውን ኮንከሪት ፓይፕ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
ብዛት |
መለኪያ |
የማስረከቢያ ቦታ |
ምርመራ |
|
1 |
ኮንክሪት ፓይፕ ባለ 48 ኢንች |
በቁጥር
|
3,500.00
|
ከጅጅጋ ከተማ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የፕሮጀክቱ ካምፕ |
|
ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትርበሥራ ሰአት የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ብር በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000322267979 ገቢ በማድረግ ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ግዥ ከፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል
ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ አለባቸው
በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በመንግስት የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በኤጀንሲው ድረ ገጽ የተመዘገቡበትን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር )በባንከ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማቅረብ
ይኖርባቸዋል::
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየርላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ይዘጋል በዚሁ እለትም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ -
- ስለ ተፈለገው ኮንክሪት ፓይፕ ዝርዝር (ሙሉ) መረጃ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስበስጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ 025111-13-13 /0927636126/0919008017
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
