Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በድርጅቱ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ዘመናዊ G+2 ሁለገብ አገልግሎት መስጫ ሕንፃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለ3 (ሦስት) ዓመት በሚቆይ እና ከ3 ዓመት በኋላ አከራይና ተከራይ በሚያደርጉት ስምምነት የኪራይ ዘመኑ ሊራዘም ወይም ሊቋረጥ በሚችልበት አግባብ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡


ለተለያየ አገልግሎት የሚከራዩ ንብረቶች ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር OR 01/2018

 

ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በድርጅቱ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ በተለምዶ ማንጎ ወይም ጊዮርጊስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሐይቁ በቅርብ ርቀት ላይ ዘመናዊ G+2 ሁለገብ አገልግሎት መስጫ ሕንፃ በማስገንባት አገልግሎት ላይ ያዋለ ሲሆን ቅርንጫፉ ከሚገለገልበት ውጪያሉ ቢሮዎችን፤ ቴራሶችን እና ባዶ ቦታዎችን እና የመሳሰሉትን ለቢሮ ለሱቅ፤ ለካፍቴሪያ፤ ለሬስቶራንት፤ ለባንክ፣ ፤ለቡና መስተንግዶና ለጅምናዚየም እና መሰል አገልግሎት እንዲውሉ ባሉበት አሁናዊ ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ 3 (ሦስት) ዓመት በሚቆይ እና 3 ዓመት በኋላ አከራይና ተከራይ በሚያደርጉት ስምምነት የኪራይ ዘመኑ ሊራዘም ወይም ሊቋረጥ በሚችልበት አግባብ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ለመከራየት እድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ፍላጎቱና አቅሙ ያለው ማንኛውም ሰው/ድርጅት በኢትዮጵያ ሕግ የተቋቋመና የሥራ ፍቃድ ያለው ወይም ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለሆነ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከተወዳዳሪዎች ውስጥ ከጨረታው የመነሻ ዋጋ በላይ ላቀረበ ተወዳዳሪ በኪራይ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ወይም በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ሕጋዊ ውክልና ያለው አካል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ሐምሌ 22 ቀን 2018 . ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ዝርዝር ጉዳይ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከባሕር ዳር ቅርንጫፍ በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላል፡፡

ለኪራይ ጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን መመልከት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ ኮፒ በመያዝ ዘወትር በድርጅቱ የሥራ ሰዓት ማለትም ከሰኞ እስከ ዓርብ ከቀኑ 300 እስከ 1000 በባሕር ዳር ከተማ የድርጅቱ ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት መመልከት ይችላል፡፡

የጨረታውን ሰነድ የገዛ ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን ያሰፈረበትን የጨረታ ሰነድ ከሐምሌ 22 ቀን 2018 . ጀምሮ እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2018 . ባሉት ተከታታይ ቀናት እና የጨረታ ሳጥኑ እስከ ሚታሸግበት ነሐሴ 6 ቀን 2018 . እስከ 800 ሰዓት በባሕር ዳርቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሠዓት 800 ተዘግቶ በዚሁ እለት 830 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ወይም አስገዳጅ ነገር ሲገጥመው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

 ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918765584 ወይም 0953680904 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ የባሕር ትራስፖርትና ሎጀስቲክስ

Save Tender