Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
  • Address ኮተቤ ብረታ ብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-42-95
  • Websitehttps://www.eep.com.et/?lang=am
  • Deadline31 Jul 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening date2026-08-18 14:30:00
  • Categories Wood And Wood Working , Firewood

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባለበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢሼአ/ንአ/ግጨ-03/2019

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባለበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሎት

የሚወገደዉ ንብረት ዓይነት

የሚገኝበት ቦታ

መለኪያ

 

ብዛት

 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ

የጨረታ መክፈቻ

1

የምሰሶ ተረፈ ምርት ቁርጥራጭ እንጨቶች

ጎተራ

በሜ.ኩ

465

30000

ነሐሴ12 ቀን 2018 8:00

ነሐሴ12 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 8:30

2

የምሰሶ ተረፈ ምርት ቁርጥራጭ እንጨቶች

ነቀምት

 

15

6000

ነሐሴ12 ቀን 2018 8:00

 

ነሐሴ12 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 8:30

 

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበርበፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን፤ መስፈርቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

1.  በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው _ ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

2.  ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ፡፡

3.  ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
4.
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው::

5.  ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና(Bid Security) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም .. በማሰራት የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡

6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታዉን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ፡፡

7.  ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።

8.  በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ ከሚገለፅበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፋችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት የመፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ... ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፡፡

9.  ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊደረግ ይችላል፡፡

10. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. የኦከሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክመስመር 09-05-11-55-1 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

12. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር on-1-11-98-97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

Save Tender