Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአቃቂ ቃሊቲ የሚገኘው 2B-G-10 ሁለገብ ህንፃ ባለበት ሁኔታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለቢሮ፣ ለመኖሪያ እና ተዛማጅ ለሆኑ አገልግሎቶች ማከራየት ይፈልጋል፡፡


የህንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአቃቂ ቃሊቲ የሚገኘው 2B-G-10 ሁለገብ ህንፃ ባለበት ሁኔታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለቢሮ፣ ለመኖሪያ እና ተዛማጅ ለሆኑ አገልግሎቶች ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ስራ ቀናት ውስጥ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት መወዳደርይችላሉ፡፡

1.     አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብርየከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤

2.     የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/በመከፈል ከሐምሌ 24 ቀን 2018 ..እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2018 .. ዘወትርከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 230 እስከ ቀኑ 630 እንዲሁም ከሠዓት ከቀኑ 730 እስከ 1130 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 230 እስከ ቀኑ 630 በቅሎ ቤት ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ //ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መግዛት ይችላሉ፤

3.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ህንፃው የሚገኝበት ቦታ በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ፤

4.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2018 .. ከጠዋቱ 430 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

5.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በሲ..

1.     ጌረታ ማስታወቂያ

2.     ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፤

6.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ማሳየት አለባቸው፤

7.     ጨረታው ነሐሴ 18 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው /ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፤

8.     ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው የድርጅታቸውን ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፤ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤

9.     ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሰጡትን ዋጋ መለወጥም ሆነ ማሻሻል አይችሉም፤

10.                        የጨረታው አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸው በተገለፀ 10 /አሥር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልተዋዋሉ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተወርሶ ኮርፖሬሽኑ ሌላ አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፤

11.                        ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

12.                        ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0114-16-34-83 መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ፡- በቅሱ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ስፊት

ስልክ ቁጥር፡- 0114-16-34-83

አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ

 

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
- The Ethiopian Trade Works Corporation is tendering the lease of the 2B-G-10 multi-purpose building in Akaki Kality to legally licensed organizations, for office, residential, and related services under a two-year renewable contract. - Bid document price: ETB 1,000 (non-refundable). Bid bond: ETB 10,000 via CPO or unconditional bank guarantee. - Submission deadline and bid opening: 2026-08-24. - Eligibility: valid renewed business license, trade registration, paid current taxes, and taxpayer identification certificate; 15% VAT must be shown in the price proposal form.
Save Tender