በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ ለ02(ሁለት አመት) የሚውል የጥበቃ አገልግሎት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ድ/ዳ/ድ/ጮ/ሆ/01/19
በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ ለ02(ሁለት አመት) የሚውል የጥበቃ አገልግሎት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
1. ተጫራቾች በዘርፉሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2019 ዓ/ም ግብር የከፈሉ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. በመንግስት ግዢ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡብትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ከፌደራል ፖሊስ የታደሠ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No.) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00(አንድ ሺ ብር) በመክፈል በድል ጮራ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር A/02 በመቅረብ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
5. መስፈርቱን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተመስከረለት ቼክ ወይም(CPO) ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4:00 ሠዓት ተዘግቶ ከቀኑ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታለግዢ ፋ/ን/አስ/ዳይሮክትሬ ቢሮ ቁጥር A/02 ይከፈታል።
8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈራረም አለበት:: ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
9. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፤ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
10. ከግል ስራና አገናኝ ኤጀንስ በአገር ውስጥ ስራና ሠራተኛ የማገናኘት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል
ስልክ ቁጥር፡- 025-211-5692 / 0982 540 408 / 0901 103 211 ፤ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 177
የድል ጮራ ሆስፒታል
