ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ-1 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ወይም ጠቅላላ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ (GC- 1/GWWC-1) የሆኑ ሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ እንዲሁም የዝናብ ውሃ ማፋሰሻ መስመር የዲዛይን ግምገማና ዝርጋታ ፕሮጀክት ስራን ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T629
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ-1 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ወይም ጠቅላላ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ (GC- 1/GWWC-1) የሆኑ ሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ እንዲሁም የዝናብ ውሃ ማፋሰሻ መስመር የዲዛይን ግምገማና ዝርጋታ ፕሮጀክት ስራን ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
1. የፕሮጀክቱ ግንባታ ሥራው 540 ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት።
2. ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሸን ባለስልጣን ለ2018 ዓ.ም የታደሰ በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ-1 ወይም ጠቅላላ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ደረጃ-1 (GWWC-1/GC-1) የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-629 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኃላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
6. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፡-
ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ +251 11-517-8918
ኢ-ሜይል: ESAYASTS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
