የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ የተለያዩ አይነት የንብ እርባታ እና የዶሮ እርባታ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ድጋሚ የወጣ የንብ እና ዶሮ እርባታ ቁሳቁሶች ግዥ ጨረታ
ማስታወቂያ 15/2019
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ የተለያዩ አይነት የንብ እርባታ እና የዶሮ እርባታ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የዕቃዉ አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ጨረታ የሚዘጋበትና ሚከፈትበት ሰዓት |
ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ |
|
1 |
ሎት1 |
የተለያዩ አይነት የንብእርባታ ቁሳቁሶች |
በጥቅል |
1 |
50,000 |
በ31ኛዉ ቀን በ4፡00ታሽጎ በዕለቱ 4፡10 ይከፈታል። |
ደ/ኢ/ግ/ቢሮ ዲላ መህህራን ኮለጅ ግቢ |
|
2 |
ሎት2 |
የተለያዩ አይነት የዶሮ እርባታ ቁሳቁሶች |
በጥቅል |
1 |
50,000 |
ንግድ ስራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
v ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
v በተጫራቾች የሚቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒ-አ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው::
v ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 30ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ወስጥ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት ከፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
v ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና እንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ አዘጋጅቶ በማሸግና ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ከቶ በማሸግ በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በቢሮው ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4:10 ተጫሪቶች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ ንብ አስ/ዳይሬከቶሬት ከፍል ይከፈታል፡፡
v ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
v የጨረታው መክፈቻ ቀን ማለትም 31ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
v ከአንድ በላይ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋ እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል።
v ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበስጠ መረጃ:- 046-131-0134 /0916176573 ይጠቀሙ::
የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት ግብርና ቢሮ
