Tender Detail

Tender Details


ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. በተለያየ ወቅት የሚያካሂዳቸውን ዓመታዊ መደበኛ፤ እንዲሁም ሌሎች ያልታቀዱ ድንገተኛ ሁነቶችን በፎቶ እና በቪድዮ በከፍተኛ ጥራት በመቅረጽና ኤዲት በማድረግ የሚያስረክበው ድርጅት አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ለአንድ ዓመት የሚቆይ ውል (ኮንትራት) መፈራረም ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ቁጥር፦ ሕብርት /ጨረታ/26-27/012

የፎቶ እና ቪድዮ ቀረጻ አገልግሎት ግዢ ጨረታ

ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. በተለያየ ወቅት የሚያካሂዳቸውን ዓመታዊ መደበኛ፤ እንዲሁም ሌሎች ያልታቀዱ ድንገተኛ ሁነቶችን በፎቶ እና በቪድዮ በከፍተኛ ጥራት በመቅረጽና ኤዲት በማድረግ የሚያስረክበው ድርጅት አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ለአንድ ዓመት የሚቆይ ውል (ኮንትራት) መፈራረም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የታደሰ ንግድ ፍቃድ’ ቲን ሰርተፍኬት’ ¾}ÚT] እሴት ታክስ ምዝገባ እና የሙያ ፍቃድ እንዲሁም አገልግሎቱን የማቅረብ ልምድ ያላቸውን ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች ስለ አገልግሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ሰዓት ቴዎድሮስ አደባባይ አከባቢ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ገንዘብ ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ.) በሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ስም በማዘጋጀት ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ለሥራው የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች በማሟላት በሕግ ፊት ዉል መፈፀም የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የተሟላ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከዋጋ ማቅረቢያ እና ደጋፊ የሥራ ልምድ ማስረጃዎች (በቴክኒካል እና ፈይናንሺያል ሠነድ) ለየብቻ በማድርግ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቴዎድሮስ አደባባይ አከባቢ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ሕንፃ 9ኛ ፎቅ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው በዕለቱ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ሕንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ  መረጃ  በስልክ  ቁጥር +251 11 1 26 34 34 የውስጥ መስመር                    160,402,190 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

Save Tender