የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
የሸቀጥ ግዥ ጨረታ (ቁጥር 002/2019)
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- አንደኛ ደረጃ የበለፀገ የዳቦ ዱቄት CES 309፡2022
- ፓስታና መኮረኒ CES 1055፡2022
- ሩዝ ES ISO 7301:2022
- ከሸንኮራ አገዳ የተመረተ ስኳር ICUMSA 45 (SUGAR CANE)
- ፈሳሽ የሱፍ ዘይት (CES 17:) and labeling CES 73
- የተለያየ መጠን ያላቸው የብርድ ልብስ ምርቶች (ES 3840:2015)
- የተለያየ መጠን ያላቸው ፎጣዎች
- የፕሪንተር ወረቀት (ES 3735-15:2020)
- የቤት ክዳን ቆርቆሮ (CES 40:2024)
- የቆርቆሮ እና ግድግዳ ሚስማር (CES 33:2023)
- የተለያየ መጠን ያላቸው የልብስ ማጠቢያ ሳሙናዎች CES42:2024
በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ለሩዝ፤ ስኳር፤ ፈሳሽ ዘይት እና ፕሪንተር ወረቀት አምራች ወይም አስመጭና አከፋፋይ እንዲሁም ለተቀሩት ምርቶች አምራች ብቻ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፤ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርቴፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት) ለብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን (financial) እና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች (technical) በተለያየ የታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡10 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓቱ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር 0113692436
