Tender Detail

Tender Details

  • Company የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0113 360 162
  • Website
  • Deadline27 Aug 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 100 (የማይመለስ)
  • opening date20ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Vehicle (Garage Service)

የተሽከርካሪዎች ጥገና ጨረታ


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር GGWW/0002/2019

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ማለትም፡-

  • ሀርድ ቶፕ ፒካፕ ሲንግል ጋቢና D4D ሂኖ መኪና አንቡላንስ መኪኖች በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች
  1. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫትና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የጋራዥ ተሽከርካሪ ጥገና የምስክር ወረቀት በኦንላይን /online/ ሲስተም የተመዘገበ መሆን አለበት።
  3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታው ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡ ሀ/ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 20000(ሀያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ፡ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ሀያ/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት።
  7. የጨረታው ሰነድ 20ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ደግሞ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

  1. በግዢ ኤጀንሲ በዘርፉ ማስጠንቀቂያ የተሰጠባቸው ድርጅቶችም መወዳደር አይችሉም
  2. ተጫራቾች የጥገና የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ውል የምንቋርጥ መሆኑን እንገልጻለን።
  3. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0113 360 162 / 0113 360 146

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
- The Gedebano Guta Zer Woreda Finance Office (Central Ethiopia Region, Guraghe Zone) invites bids for the maintenance and repair of its vehicles, including hard top single cab pickups, D4D Hino vehicles, and ambulances. - The bid document costs a non-refundable 100 ETB; bidders must submit a bank-guaranteed CPO of 20,000 ETB as bid security. - Submission closes on the 20th consecutive working day at 8:00 AM, with opening on the same day at 8:30 AM. - Bidders must have a valid trade license, be registered for VAT and TIN, hold an online-registered garage vehicle maintenance certificate, and provide legal authorization if submitting as representatives. - Organizations that have been formally warned by the procurement agency are not eligible to compete.
Save Tender