Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address በምስራቅ ሸዋ ዞን ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462 -114-616
  • Website
  • Deadline25 Aug 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500 /አምስት መቶ/ (የማይመለስ)
  • opening dateከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Steel, Metals And Aluminium

የተለያየ መጠን ያላቸው የማጠናከሪያ ብረቶች ግዥ


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢመአ/ሻሽ/ዐዐ1/2019

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለ2019 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የማጠናከሪያ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠብቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  4. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ዕቃ ግዥ/አ/ን/አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
  7. በጨረታው መከፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462-114-616 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
- Open tender for the procurement of various sizes of reinforcing steel for road maintenance and construction for the 2019 budget year, issued by the Ethiopian Roads Administration, Shashemene Road Maintenance District (Oromia), tender no. ኢመአ/ሻሽ/ዐዐ1/2019. - The notice will remain for 15 consecutive days in Addis Zemen; bids close on the 16th working day at 8:00 PM and open at 8:30 AM, with opening postponed to the next working day if the date is a holiday. - Non-refundable bid document fee: 500 ETB, payable to Commercial Bank of Ethiopia account 1000002579859; bid bond: 50,000.00 ETB in the form of a bank-confirmed CPO, attached to the bid document (insurance or other forms not accepted). - Bidders must provide a renewed 2018 E.C. trade license registration certificate, VAT certificate, taxpayer certificate, and 2017 budget year tax clearance, and submit financial and technical documents as 1 original and 2 copies in separate envelopes.
Save Tender