Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address ሞያሌ : ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0464441415
  • Website
  • Deadline17 Aug 2026, 9:45 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ግልጽ እና ሀራጅ ሰነድ
  • opening date4፡00
  • Categories Other , Vehicle , Cosmotics

የሞተርሳይከል እና የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ኮስሞቲከስ፣ የንፅህና መጠበቂያ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ነዳጅ፣ ምግብ ነክ ዕቃዎች፣ የጥራጥሬ እህሎች እና ሌሎች ዕቃዎች መኪናን ጨምሮ በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ መሸጥ


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 45/2018

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተርሳይከል እና የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት ዕቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የመገናኛ መሳሪያዎች ኮስሞቲከስ እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ነዳጅ፤ ምግብ ነክ ዕቃዎች የጥራጥሬ እህሎች እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች መኪናን ጨምሮ በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመሁኔታዎች እና መስፈርቶች የሟሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን ከሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክርወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  2. ተጫራቾች የግልጽ እና ሃራጅ ጨረታ ሰነድ በቴሌግራም አካውንት የሚላከላችሁ ሲሆን ተጫራቹ ለመግዛት ዘወትር በስራ የሚፈልገውን የዕቃ ዝርዝር ያለበት ገጽ እና የጽ/ቤቱ ማህተም ሳይቆረጥ ፕሪንት በማድረግ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ግልጽ እና ሀራጅ ሰነድ ብር100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር16 ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ (RV) በመቀበል ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ሌሎች ከላይ የተገለጹ አስፈላጊ ሰነዶች እንዲሁም RV (ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ) ጭምር በማያያዝ ወደ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወከሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዘኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዝግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
  7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
  10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ለመ/ቤቱ ግቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464441415/0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
- Open and auction tender sale of seized/confiscated goods including motorcycles and vehicle spare parts, clothing, electronics, communication equipment, cosmetics, sanitary items, household goods and decorations, fuel, food items, grains, and other items including vehicles. - Issued by the Ethiopian Customs Commission, Moyale Branch Office (Tender No. 45/2018); posted on 13 August 2026. - Samples may be inspected from the publication date through the 7th day at Moyale and sub-station warehouses; the tender closes on the 8th day at 3:45 AM (local time) and opens at 4:00 AM, moving to the next working day if the 8th day is not a working day. - Bid documents cost a non-refundable 100 ETB each; bid security is a 5% bank-confirmed CPO for open tender, while the CPO amount for auction items varies by item code per the tender rules. - Bidders must hold a renewed trade license related to the goods, a VAT registration certificate, proof of current tax payment, and a recent VAT activity certificate with their tax ID number attached to the bid documents.
Save Tender