Tender Detail

Tender Details

  • Company Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)
  • Address ዋና መ/ቤት የድሮ መርከብ ሕንፃ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አጠገብ ያለው ሕንፃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115539535
  • Websitehttps://www.fhc.gov.et/en#New
  • Deadline26 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price500.00(አምስት መቶ ብር)
  • opening dateነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15
  • Categories Electronics Materials

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሊፍት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕታ/02/12/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕቃ/02/12/2018


1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሊፍት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕታ/02/12/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
2. ለኮርፖሬሽኑ ለሊፍት ጥገና አገልግሎት የሚያገለግል የተለያዩ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴከኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተ.ቁ

የእቃ ዝርዝር

የጨረታ ማስከበሪያ

1

የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ

50,000.00


3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልከቶ በፌዴራል መንግስት ባለቤትነት የተያዙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1070/2017 ሲሆን ከሚፈለገው የኤሌከትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል፡፡

4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው የኮርፓሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክበተመሰከረለት የባንከዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መከፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬክተር ከኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


ለተጨማሪ መረጃ
ዌብሳይት/Website WWW.agh.gov.et
የፖ.ሳ.ቁ. Р.О. Box 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
Federal Housing Corporation seeks bids for procurement of electro-mechanical items for elevator maintenance. Bidders must submit technical and price documents in separate sealed envelopes, hold a renewed trade license, and provide tax clearance.
Save Tender