Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባሕር ዳር ሪጅን (Ethiopian Electric Service Bahir Dar Region)
  • Address ባህርዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0583206999
  • Website
  • Deadline27 Aug 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • opening dateAugust 27, 2026, 02:30pm
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢኤአ ባሪ/ግብጨ/001/2019

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ከዚህ በታች የተገለጹትን አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ነሐሴ 16 ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ባሕር ዳር በሚገኘው በሪጅኑ ዋና መ/ቤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 408 በመምጣት ለአንዱ ሎት ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  2. በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ብረት በማቅለጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ፋብሪካዎች ወይም ከብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች ህጋዊ ውክልና የሚያቀርቡ ብቻ ናቸው።
  3. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ጨረታው ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት በሰፕላይ ቼይን፣ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 408 ይከፈታል።
  7. ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 058-320-6999/6776 መደወል ይችላሉ።
  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባሕር ዳር ሪጅን

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Service Bahir Dar Region is selling various non-operational metals via open tender, as-is and at their current locations. Participation is limited to metal smelting factories or their legal representatives. Bidders may inspect the assets on business days.
Save Tender