የግልፅ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
1ኛ ዙር መለያ ቁጥር 001/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ወረገኑ ቅደመ አንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሎት ዝርዝር ይሆናሉ፡፡
| ተ.ቁ | የሎት ዝርዝር | የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ ብር |
| 1 | የደንብ ልብስ | 20,000 |
| 2 | የስፖርት ትጥቅ | 20,000 |
| 3 | አላቂ የቢሮ ዕቃዎች | 40,000 |
| 4 | አላቂ የፅዳት ዕቃዎች | 40,000 |
| 5 | የሕንፃ ቁሳቁስ መግዣ | 60,000 |
| 6 | የኤሌክትሮኒከስ መግዣ | 65,000 |
| 7 | የትምህርት ዕቃዎች | 30,000 |
| 8 | የሕክምና ዕቃዎች | 10,000 |
| 9 | ሕትመት | 10,000 |
| 10 | ልዩ ልዩ መሣሪያዎች | 10,000 |
| 11 | የኤሌክትሮኒከስ ጥገና | 10,000 |
| 12 | የሕንፃ ቁሳቁስ ጥገና | 10,000 |
| 13 | የጭነት አገልግሎት | 10,000 |
| 14 | የትራንስፖርት አገልግሎት | 10,000 |
| 15 | ምንስትርምንግ /ልዩ ልዩ | 10,000 |
* ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳዲሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገንዘብና በኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር/200.00/ ሁለት መቶ ብር በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር (3) እየቀረቡ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቶች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር (ተከታታይ የሥራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር (3) ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበት የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸዉ::
- የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን 11:30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በቀጣይ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው 4፡00 ሰዓት ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ የተጠቀሰውን ብር ከባንክ በተረጋገጠ /CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው የማይቀረብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ 10% ከባንክ የተረጋገጠ /CPO/ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ወረገኑ ቅደመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ስልክ ቁጥር 0118669955/0924264427 ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈጬ የሚወስድ መንገድ ወደ ቀኝ 3 ከሎ ሜትር ላይ ይገኛል፡፡
ቦሌ ወረገኑ ቅደመ አንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for supplying goods and services to Bole Weregenu Primary and Middle School, including uniforms, sports gear, office/cleaning supplies, building materials, electronics, medical items, printing, maintenance, and transport. Bidders need valid licenses, tax clearance, and supplier registration.
