የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ብሄራዊ ቲያትር አካባቢ በቤት ቁጥር 287/14 የሚገኘው ልዩ ስሙ ኦፊሶል ህንጻ ላይ ምድር ወለል 74.30ካሬ ፣መዳረሻ (አንደኛ ፎቅ) 74.00 ካሬ እና ከምድር በታች 86.23 ካሬ ለተለያዩ አገለግሎቶች የሚውል ሁለገብ ቢሮ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ጨረታ ቁ. ፋሀአዳ/ግዳ/026/2018
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ብሄራዊ ቲያትር አካባቢ በቤት ቁጥር 287/14 የሚገኘው ልዩ ስሙ ኦፊሶል ህንጻ ላይ ምድር ወለል 74.30ካሬ ፣መዳረሻ (አንደኛ ፎቅ) 74.00 ካሬ እና ከምድር በታች 86.23 ካሬ ለተለያዩ አገለግሎቶች የሚውል ሁለገብ ቢሮ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
- ድርጅታችን ለኪራይ ያቀረባቸውን ክፍሎች በጨረታ መወዳደር/ መሣተፍ የሚፈልግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 9፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ክፍል በኢትዮጵያ መድን ድርጅት (Ethiopian Insurance Corporation) ስም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ወይም ለዘጠና ቀናት በሚቆይ ቅድመ ሁኔታን ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. በድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ግዥ ዳይሬክቶሬት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-5512400 የውስጥ መስመር 237/262 ወይም በቀጥታ 011-5504931 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኢትዮጵያ መድን ድርጅት
