ፀደይ ባንክ አ.ማ አቶ ለማ ተፈራ ሶሪ ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍጹ ከተማ የካርታ ቁጥር OR003075014013 በአቶ ጌታሁን ወዳይ ደረሰ ተመዝግቦ የሚገኘዉን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለ ሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ አቶ ለማ ተፈራ ሶሪ ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍጹ ከተማ የካርታ ቁጥር OR003075014013 በአቶ ጌታሁን ወዳይ ደረሰ ተመዝግቦ የሚገኘዉን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ መጫረት እንዲችሉ ይጋብዛል፡-
- የቤቱ የጫረታ መነሻ ዋጋ ብር4,609,650.62 /አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠኝ ሽህ ስድትስ መቶ ሃምሳ ብር62/100/
2.ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጫረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3.የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል፡፡
4.በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት፡፡
5.የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
6.በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
7.የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል/፡፡ ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል፡፡
8.ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
9.ጫረታዉ የሚካሄደዉ መሰከረም 05/2019 ከጠዋቱ 3.00—5.00 የተጫራቾች ምዝገባ፤ ከ5.00 እስከ ቀኑ 6.00 ሰዓት ጫረታ በኦሮሚያ ክልል ጨለለቃ ክ/ከተማ ቢሾፍቱ ሆዳነቢይ ህንፃ ይሆናል፡፡
10.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ በስ.ቁ 01143303062/0912292609 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
