Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን
  • Address ወልቂጤ ከተማ ወደ ወልቂጤ ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ላይ የድሮው የወልቂጤ ከተማ ስፖርተኞች ማደርያ ጊቢ ውስጥ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 011 365 9932
  • Website
  • Deadline01 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (ሦስት መቶ) ብቻ (የማይመለስ)
  • opening date16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Rent , Construction Machinery , Construction Vehicle

የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ክራይ አገልግሎት ግዥ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/መ/ባ/ማሽ/001/19

 

መ/ቤታችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በስሩ ባሉ ዲስትሪክቶችና አከባቢያቸው የመንገድ ፕሮጀከቶች አገልግሎት የሚውል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ማለትም ዶዘር፣ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ሮለር፣ሎንግ ቤዝ መኪና እና ፒክ አፕ መኪና ክራይ አገልግሎት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

 በመሆኑም፡-

1.      1.ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም አገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.    ተጫራቾች የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን አንድ ዋና እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦሪጂናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበርያውን በተለየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) ብቻ በመከፈል በባለሥልጣኑ ዋና መ/ ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

4.    የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።

5.    አቅራቢዎች ጨረታውን ገቢ የሚያደርጉት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይሆናል።

6.    ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅድመ-ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) ለእያንዳንዱ ማሽን ብር 10,000.00(አስር ሺህ) ብቻ ሲሆን ለሎንግ ቤዝ መኪና እና ፒክ አፕ መኪና ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000(ሀምሣ ሺህ) በማሰራት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በኢንሹራንስ ዋስትና የሚቀርብ የጨረታ ማስከበርያ ተቀባይነት የለውም።

7.    ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

8.    መ/ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.    ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም

ስልክ ቁጥር፡- 011 365 9932

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን

✨ messages.ai_summary
Procurement of crane rental services for construction machinery—dozers, graders, excavators, rollers, long-base trucks, and pickups—for road projects. Bidders must hold valid business licenses, supplier certificates, and VAT registration. Tender open to all nationalities.
Save Tender