Tender Detail

Tender Details


በቡኖ በደሌ ዞን የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ህጋዊ የሆኑና መስፈርት የሚያሟሉ ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በከተማዉ ዉስጥ ለሚገኙ ሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፤ የቢሮ ዉስጥ ፈርኒቸሮች፤ የተለያዩ የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች የዉሀ እቃዎች ፤ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች እና ባጃጅ፤ የሠራተኞች ደንብ ደንብ ልብስ ልብስ እንዲሁ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በቡኖ በደሌ ዞን የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ህጋዊ የሆኑና መስፈርት የሚያሟሉ ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በከተማዉ ዉስጥ ለሚገኙ ሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፤ የቢሮ ዉስጥ ፈርኒቸሮች፤ የተለያዩ የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች የዉሀ እቃዎች ፤ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች እና ባጃጅ፤ የሠራተኞች ደንብ ደንብ ልብስ ልብስ እንዲሁም እንዲ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪ ጎማዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡

መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች በእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለዉና 2018 ዓ.ም ግብር ከፍሎ የ2019 ዓ.ም ንግድ ፈቃዱን ያደሰ ወይም ከገቢዎች ፅ/ቤት ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለዉና ማቅረብ የሚችል፡፡
1. የቫት (15 %) ተመዝጋቢ ሆኑና ማስረጃዉን ማቅረብ የሚችል፡፡
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር መዝገብ ላይ የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
3. በመንግስት ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ያልተከለከለ እና የተከለከለ ከሆነ የጊዜ ገደቡን የጨረሰ፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳነዱ የ ጨረታ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በስንቄ ባንክ ለበደሌ ከተማ ፋይናንስ አካዎንት ቁጥር 1071291641810 ገቢ በማድረግ ኦርጅናል ባንከ ስሊፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. በዚህ ማስታወቂያ ላይ ከተ.ቁ 1 – 4 የተዘረዘሩት ማስረጃዎች መኖራቸዉን የሚያሳይበግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ በአንድ ፖሰታ ዉስጥ ታሽገዉ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. የሚገዙ ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠዉ መሰረት የሚያቀርቡበትን ዋጋ ቫትን (15 %) ጨምሮ በጥንቃ ቄ በመሙላት በአንድ ፖሰታ ዉስጥ ታሽገዉ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን _ ዉስጥ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. አንድ ተወዳዳሪ ለአንድ ዓይነት ዉድድር ሁለት (2) ፖስታ ማስገባት ያለበት ሲሆን የመወዳደሪያ መስፈርቶች ያለበትን ፖስታ የቴከኒክ በማለት እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሞላዉ የ ዋጋ መወዳደሪያ ያለበት ፖስታ ላይ የፋይናንስ (financial) በማለት ተለይቶ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
8. ለማንኛዉም አይነት ጨረታ የሚሞላዉ የመወዳደሪያ ዋጋ ከነቫት መሞላት አለበት በዚሁ መሰረት ቫት (15%) ሳይጨመር የተሞላ _ ወይም ቫት ያስጨምራል _ ተብሎ የማይሞላ ዋጋ ቫት እንዳለዉ ይወሰዳል፡፡
9. ማንኛዉም ተወዳዳሪ በዋጋ ማቅረቢያዉ ላይ ፊርማዉንና የድርጅቱን መህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ስርዝ ድልዝ ያለዉ የቴከኒከም ሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም፡፡
11. ማንኛዉም ተወዳዳሪ በጨ ረታዉ ያሸነፈባቸዉን እቃዎች በራሱ ወጪ ጭኖ እስከ በደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ ቤት በማምጣት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

12. የሠራተኞችን ደንብ ልብስ ለማቅረብ የሚወዳደር ማንኛዉም ተወዳዳሪ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የልብስ ዓይነቶች የሚያሳይ ግልጽ የሆነ ናሙና ጨረታዉ በሚከፈትበት ጊዜና ቦታ ይዘዉ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
13. በዚሁ መሰረት ሕጋዊ የሆኑና አስፈላጊዉን መስፈ ረት የምያሟ ላ ማንኛዉም ነጋዴ ይህ ማታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀን መካከል የበደሌ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በመሄድ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ የበደሌ ከተማ ገንዘብ የግዢና ንብረት አስተዳደር ከፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት በማምጣት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ በመዉሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
14. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ15 ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
16. ማሳሰቢያ፡- ስለ _ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0474452385 ላይ በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡


የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት 

✨ messages.ai_summary
Open tender for legal, qualified suppliers to provide office stationery, cleaning supplies, furniture, electronics, water equipment, motorcycles, bajaj, staff uniforms, vehicles, and machinery tires for sector offices in Bedele town. Bidders must have valid trade licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registry proof.
Save Tender