Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 251-011-1-25-07-33
  • Website
  • Deadline29 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • opening dateበዕለቱ ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት
  • Categories Vehicles Rent , Event Organizing And Planning , Catering And Cafeteria Services

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የኢቨንት ኦርጋናይዘር አገልግሎት፡ የሰራተኞች ካፌና የመኪና ኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የኢቨንት ኦርጋናይዘር አገልግሎት፡ የሰራተኞች ካፌና የመኪና ኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፡ ኦንላይን የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት፡ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000-70-96-80-882 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን አካውንት ላይ አስገብታችሁ ደረሰኙን ይዛችሁ በመምጣት ሰነዱን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 706 ማግኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ከዚህ በታች በሰንጠረዡ በተገለፀው የዕቃዎች ምድብ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
ሎት ቁጥር የእቃ ምድብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
ሎት1 የኢቨንት ኦርጋናይዘር አገልግሎት 100,000.00
ሎት2 የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት 20,000.00
ሎት3 የመኪና ኪራይ 20,000.00
  1. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን በየሎቱ በመከፋፈል ቴክኒካል ኦሪጅናል ኮፒ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  3. በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በሚገኙበት ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት 2ኛ ፎቅ በሚገኘው በኮሚሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-
አራዳ ክ/ከተማ፡- አራት ኪሱ ተረስት ሆቴል 7ኛ፡ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፡- 251-011-1-25-07-33
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Tourism Commission seeks bidders for event organizing, staff cafeteria, and vehicle rental services. Bidders must hold renewed business licenses, VAT registration, online supplier registration, tax clearance, and taxpayer ID. Three lots available.
Save Tender