የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) በፊላሚንጎ አካባቢ በሚገኘው ጌት ሃውስ ሕንፃ በጀርባ በኩል ካለው የባንኩ ቢሮ ከ3ኛ እስከ 8ኛ ፎቅ ድረስ ተገጥመው የሚገኙ ያገለገሉ የተለያዩ አሉሚኒየም ፓርቲሽኖችንና ቴምፐርድ ግላስ ፓርቲሽኖችን ሙሉ በሙሉ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር FA- 02/2026/27
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) በፊላሚንጎ አካባቢ በሚገኘው ጌት ሃውስ ሕንፃ በጀርባ በኩል ካለው የባንኩ ቢሮ ከ3ኛ እስከ 8ኛ ፎቅ ድረስ ተገጥመው የሚገኙ ያገለገሉ የተለያዩ አሉሚኒየም ፓርቲሽኖችንና ቴምፐርድ ግላስ ፓርቲሽኖችን ሙሉ በሙሉ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። አሸናፊው ተጫራች ንብረቶቹን በራሱ ወጪና ኃላፊነት ፈታትቶ ማንሳት ይኖርበታል።
ተጫራቾች የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያዎች መከተል አለባቸው፦
- የጨረታ ሰነድ መግዛት፦ ከነሐሴ 17 እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የግብር መለያ ሰርተፊኬት/ካርድ ይዘው በባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00 በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ ሰነዱን ቦሌ መንገድ፣ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊት ለፊት፣ ራንግ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ከሚገኘው የንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- ንብረቶችን መመልከት፦ የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ከነሐሴ 18–22 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከ3፡00–10፡00 ሰዓት፣ ነሐሴ 23 እና 26 ቀን ከ3፡00–6፡00 ሰዓት ድረስ ንብረቶቹን በቦሌ መንገድ፣ ፊላሚንጎ፣ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ቢሮ ፊት ለፊት በሚገኘው ጌት ሃውስ ሕንፃ በአካል መመልከት ይችላሉ።
- በእያንዳንዱ ወለል ላይ ከ3 ኛ እስከ 7 ኛ ድረስ የመግቢያ በር ላይ ያሉትን ፓርትሽኖች አያካትትም፤ ከነኚህ ውጭ 8ኛን ጨምሮ ያሉት ፓርትሽኖች መሉ በሙሉ ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን የበለጠ ዝርዝሩ እና ልኬቱ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል።
- የጨረታ ማቅረቢያ፦ የዋጋ ማቅረቢያውን በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ራንግ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ፦ ተጫራቾች ከጠቅላላ የመነሻ ዋጋ፣ VAT ጨምሮ፣ 10% በCPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያልተያያዘበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- VAT፦ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ 15% VAT የተካተተበት ወይም ያልተካተተበት መሆኑን በግልጽ መግለጽ አለባቸው። ካልተገለጸ፣ ዋጋው VAT የተካተተበት እንደሆነ ባንኩ ይቆጥራል።
- ክፍያና ማንሳት፦ አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ንብረት ሙሉ ዋጋ በ5 ቀናት ውስጥ ከፍሎ፣ በራሱ ወጪና ኃላፊነት በጥንቃቄ ፈታትቶ ማንሳት አለበት። በተጠቀሰው ጊዜ ካልፈጸመ የጨረታ ማስከበሪያው CPO ይወረሳል።
- ጨረታ መዝጊያና መክፈቻ፦ ጨረታው ማክሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፤ በዚያው ቀን 8፡30 ሰዓት ራንግ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)
ስልክ፦ 011 557 6174 | ፖ.ሣ.ቁ፦ 16936
“ማህበረሰቡን ማጎልበት፣ ሕይወትን መለወጥ!”
