Tender Detail

Tender Details


ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ አዲሱ ጌትነት ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉንና ዝርዝር ሁኔታዉ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጸዉን ሸድ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ የኃራጅ ሽያጭ  ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ አዲሱ ጌትነት ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉንና ዝርዝር ሁኔታዉ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጸዉን ሸድ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ
የተበዳሪ ስም
የንብረት አስያዥ ስም
የንብረቱ መገኛ፤ደረጃና ካርታ ቄጥር
የጫረታዉ መነሻ ዋጋ
1
አቶ አዲሱ ጌትነት
አንዳሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ግንቦት 20 ክ/ከ ካርታ ቁጥር ባህኢፓ /0083/09 ስፋቱ 7000 ካ.ሜ
73‚192‚563.45

በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል፡፡

  1. የቤቱ የጫረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር 73‚192‚563.45 (ሰባ ሶስት ሚሊዮን አንድ ዘጠና ሁለት ሺኅ አምስት መቶ ስድሳ ሶስት ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም) ብቻ
  2. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል፡፡
  3. በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት፡፡
  4. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጫረታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  5. በጫረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸመል፡፡
  6. የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከሸዱ ጋር የተያያዙ ማንኛዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ወጭዎችን ገዢ ይከፍላል፡፡ ማንኛዉም ዉዝፍ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር ዉል እንዲዋዋል ይደረጋል፡፡
  7. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
  8. ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር አሰራርና መመሪያ (መመዘኛዎች) ለሚያሟላና ፍላጎት ላለዉ ተጫራች ባሸነፈበት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰላ ባንኩ እስከ 30% ( ሰላሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  9. ጫረታዉ የሚካሄደዉ መስከረም 20/2019 ዓ ም ከጠዋቱ 3.00 እስከ 6.00 ሰዓት በባህር ዳር ከተማ ጣና ክ/ከተማ ቀበሌ 16 ልዩ ቦታዉ ፀደይ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ከድሮዉ አልካን ጎን ይሆናል
  10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251115582978 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
Save Tender