Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Orthodox Church / EOC
  • Address , Phone: +251-912042979
  • Website
  • Deadline03 Sep 2026, 4:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-09-03 09:00:00
  • Categories Rent , Land, House, Building And Warehouse Rent

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን ለንግድ የሚሆን ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡


የንግድ ቤት ኪራይና የተለያዩ ለግንባታ የሚሆኑ ዕቃዎች

የጨረታ ማስታወቂያ

  1. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን ለንግድ የሚሆን ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
  2. የቤቱ አድራሻ፡- አራት ኪሎ ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የሚገኝ 3ኛ ፎቅ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 9999፣
  • ቢሮ ቁጥር 40፣41፣46፣47፣48፣
  • የቤት ቁጥር 19 በሕንጻው ምድር ቤት የሚገኝ ክፍል፣
  1. አድራሻ፡- ቸርችል ጎዳና ትንሣኤ ሕንጻ፡- የቤት ቁጥር 3 የሆነ የንግድ ቤት፣
  2. መንግሥታዊ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ተወዳዳሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ፣
  3. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ቤቱን ከተረከበ በኋላ የውሃና የመብራት ፍጆታ ራሱ ይከፍላል፡፡
  4. ድርጅቱ ለኪራይ ያቀረባቸውን ቢሮዎችና የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 1ዐ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡3ዐ እስከ 1ዐ፡ዐዐ ክፍሉን በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 5ዐ0.ዐዐ (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ ገዝቶ በመሙላት በታሸገ ኢንቫሎፕ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. ተጫራቾች በጥቅልም ሆነ በተናጥል ሲወዳደሩ የሚጫረቱበት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5ዐዐዐ.ዐዐ(አምስት ሺህ ብር) በማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከሚያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ዋጋ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ቤቱን ከፋፍሎ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይቻልም፡፡
  7. በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኢትዮፍ መጋዘን ግቢ ውስጥ የሚገኙ የግንባታ ዕቃዎች(በማንኛውም እምነት ውስጥ ያለ መጫረት ይችላል)
  8. ተጫራቾች ለንብረቱ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 6,ዐዐዐ.ዐዐ በማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከሚያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ዋጋ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  10. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2ዐዐ.ዐዐ (ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ ገዝቶ በሞሉት በታሸገ ኢንቫሎፕ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለበት፡፡
  11. ጨረታው በ1ዐኛው ቀን ከቀኑ 1ዐ፡ዐዐ ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ በ3፡ዐዐ ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
  12. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የጨረታ መነሻ ዋጋ እና ዝርዝር መመሪያ ከጨረታው ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

ለበለጠ መረጃ

በስ.. 111-57-47-99

ወይም በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ፡፡

Save Tender