Tender Detail

Tender Details

  • Company የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-450-02-22
  • Website
  • Deadline07 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazineአድስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር)
  • opening dateበዚሁ እለት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Hospitality, Tour And Travel , Vehicle tire , Vehicle Spare Parts

በአማራ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ -


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

በአማራ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ -

  • ሎት 1 የመኪና እቃ መለዋወጫዎች አመታዊ ኮንትራት ግዥ
  • ሎት 2 የመኪና ጎማ አመታዊ ኮንትራት ግዥ
  • ሎት 3 የመስተንግዶ አገልግሎት አመታዊ ኮንትራት ግዥ
  • ሎት 4 የጭነት አገልግሎት አመታዊ ኮንትራት ግዥ
  • ሎት 5 የመኪና ዘይት እና ቅባት አመታዊ ኮንትራት ግዥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል :: ስለዚህ ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TTN/ ያላቸው
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመከፈል የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡3ዐ ድረስ ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 ለመኪና እቃ 50,000/ሀምሳ ሽህ ብር/ ለሎት 2 ለመኪና ጎማ 30,000/ሰላሳ ሽህ ብር/ ለሎት 3 ለመስተንግዶ 10000/አስር ሽህ ብር፣ ለሎት 4 ለጭነት 10000/አስር ሽህ ብር/ ለሎት 5 ለመኪና ዘይት እና ቅባት 20000/ሀያ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሰ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ በማስገባት ይታሸጋል። በዚሁ እለት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅደም ተከተል በስራ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ን/አስ/ቡድን በቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ታሽጎ ይከፈታል።
  7. በጨረታው ለመጫረት የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር-033-450-02-22 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጎልም ::
  9. ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ::
  10. ውድድሩ የሚካሄደው ከሎት 1 እስከ ሎት 5 በየምድቡ በሎት ነው፡፡
  11. የእቃው ማስረከቢያ ቦታ ሎት 2 መቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በየንብረት ከፍሉ ሲሆን ሎት 1 እና ሎት 5 የመኪና መለዋዎጫ እቃዎች እና የመኪና ዘይትና ቅባት መኪኖች ለጥገና አገልግሎት ጋራጅ በሚገቡበት ጊዜ የጥገና አገልግሎት በሚሰጠው ጋራጅ /ደሴ ከተማ/ በመገኘት በባለሙያና በጋራጅ የተረጋገጠ ኦርጅናል እቃ ለንብረት ከፍል የሚያስረከብ ይሆናል እንድሁም እቃዎች በሚፈለጉበት ጊዜ በፍጥነት እና በጥራት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ እንድሁም ሎት 3 እና ሎት 4 ተቋማቶች አገልግሎት በሚፈልጉበት ቦታ እና ጊዜ በፍጥነት እና በጥራት ማቅረብና ማድረስ አለበት።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open national tender by Mekdela District Finance Office for annual contracts to supply sector offices: Lot 1 vehicle spare parts, Lot 2 tires, Lot 3 hospitality services, Lot 4 freight services, Lot 5 oil and lubricants. Bidders need valid trade license and tax ID; VAT certificate required if bid exceeds 200,000 birr.
Save Tender