የምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት በ2019 ዓ/ም ለታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውሉ ጥሬ ሰብሎችና የተለያዩ ማጣፈጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት በ2019 ዓ/ም ለታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውሉ ጥሬ ሰብሎችና የተለያዩ ማጣፈጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ እና በተወዳዳሪዎች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- ጥራት ያላቸውን የተጠየቁ ጥሬሰብሎች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
- የተለያዩ ማጣፈጫዎችን እና የዳቦ ዱቄት ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
- ለምግብ ማብስያ የሚሆን ግንድላ ማጋዶ እንጨት ማቅረብ የሚችል፤
- ተወዳዳሪዎች የተጠየቁትን ናሙና ሙሉ በሙሉ ማቅረብ አለባቸው፤
- የ2018 ዓ/ም ግብር አጠናቅቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታከስ ከፋይነት (TIN) ያላቸው፤
- ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) 50,000.00 ብር ከኦርጅናል ማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል የግዥ ከፊል ከምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዓይነቶች እንደዚሁም ኦሪጅናሉና በኮፒው ላይ በግልጽ በመጻፍ በድርጅቱ አለባቸው የድርጅቱን ስም በሚያቀርቡት ፖስታ ላይ ማህተም አና ፊርማ አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ኤንቬሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከቀኑ በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ሆኖም የተወዳዳሪዎች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግድም፤
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ገዥው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፤
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0577710193 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት
✨ messages.ai_summary
West Wollega Zone Prison seeks bids to supply raw grains, seasonings, and firewood for inmate meal preparation. Bidders must hold valid trade licenses, provide samples, have TIN and paid 2018 taxes, and deliver goods to the office.
