በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችንና አገልግሎቶችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢት/ያ ከልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችንና አገ/ቶችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ሎት-7 ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሚሆን ነጭ ሼራ ድንኳን ከነስቴጅ እና ፕላስቲክ ወንበሮች ኪራይ ሎት-15. የመድረክ መሪ ከነሙሉ ሳውንድ ስይስተም ሎት-16 የእንስሳት ዲቃላ ቁሳቁሶች ግዥ ሲሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉት።
2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉት በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገበና ለ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በ EGP የተመዘገቡ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ ሥራዎች አገልግሎቶች ከአሰሪው አካል የመልካም ሥራ አፈጻጻም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጁበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ።
4. የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል።
5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት ድረስ / ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ። ዘገይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
6. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል። 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና - ለእያንዳንዱ፡- ሎት-7 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሎት15 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ርክብክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል።
9. የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 046 180 0863 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር
ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
