የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2019 በጀት ዓመት፡- Harvesting Packing & Bagging Materials
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OSE/NCB/001/2019
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2019 በጀት ዓመት፡- Harvesting Packing & Bagging Materials
ሎት 1. የተለያዩ የዘር መቋጠሪያ ከረጢት (pp bags)
ሎት 2. የተለያዩ የምርት መሰብሰቢያ መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን
ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)፣
4. የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸውጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል። የጨረታ ሰነድ ሶፍት ኮፒ (Soft copy) መግዣ ዋጋ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን፤ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2:30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ሕንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል።
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት፤
ከሰኞ-ዓርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡30 ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ፡-
ስ.ቁ 011-416 0309/ 011-466-2527 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
