የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት1፡- ኤሌክትሮኒከስ ሎት2:- የመኪና መለዋወጫ ዕቃ
ስለዚህ ተጫራቾች፦
የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው ያላት አርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡
የንግድ ሥራ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ያለው ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣
የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ እና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሁሉም ዶከመንት ላይ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍና በመፈረም በሰም ለየብቻቸው አሽጎ ማቅረብ የሚችል፣
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 10,000 (አስር ሺህ) ብር C.P.O (ሲ ፒ.አ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስም በማሰራት ብቻውን በሰም አሽጎ ማስያዝ የሚችል፣
አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በተገለጸበት በ5 (አምስት) ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውል ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ C.P.O (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ የሚችል፣
ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩከ፤የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ሰጪዎችን በራሱ ሽፍኖ ዕቃውን ማስረከብ የሚችል ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮው ቁጥር 507 ቀርበው በመከፈል ሰነዱን በመውስድ በተዘጋጀው የጨረታ
ሠነዱ ላይ የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ፖስታውን አሽጎ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ በ15 ሥራ ቀናት ውስጥ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ ግቢ ውስጥ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ16 ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ መጫረት አይችልም።
የወቅቱን የገቢያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም። ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት።
ጨረታው የሚከፈተው በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፦ 0462125731 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ
