ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የጥራት እና የምግብ ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት (FSSC 22000 and ISO 9001:2015 (Quality and Food Safety Management System) የስልጠና እና የማማከር አገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የስልጠና እና የማማከር አገልግሎት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር EAC 041/2018
1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የጥራት እና የምግብ ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት (FSSC 22000 and ISO 9001:2015 (Quality and Food Safety Management System) የስልጠና እና የማማከር አገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ 7፡30 – 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ” ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት
v አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ፣
v አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ እንዲሁም፣
v ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
v በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የጥራት እና የምግብ ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት (FSSC 22000 and lSO 9001:2015 (Quality and Food Safety Management System)) የስልጠና እና የማማከር አገልግሎት ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 የሚከፈት ይሆናል።
6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 667 6204 ፋክስ ቁጥር 011 673 2006 መጠቀም ይችላሉ።
8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር
