የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ተጫራቾችን አወዳድሮ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ የፅዳት መጠበቅያ እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች ማለትም ለመንገድ ፅዳት፤ ለቢሮ ፅዳት፤ ለጥበቃና አትክልተኛ፣ ቋሚ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች) ፣ ሌሎች ለውበትና አረንጓዴ ተፋሰስና ለከተማ ግብርና እና ለኪራይ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችና ንብረቶች ፣ የህትመት አገልግሎቶች፣ ልብስ ስፌት፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች፣ የካፍቴሪያ አገልግሎትና የመሣሠሉትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡