በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ የፅዳት መጠበቅያ እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች ማለትም ለመንገድ ፅዳት፤ ለቢሮ ፅዳት፤ ለጥበቃና አትክልተኛ፣ ቋሚ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች) ፣ ሌሎች ለውበትና አረንጓዴ ተፋሰስና ለከተማ ግብርና እና ለኪራይ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችና ንብረቶች ፣ የህትመት አገልግሎቶች፣ ልብስ ስፌት፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች፣ የካፍቴሪያ አገልግሎትና የመሣሠሉትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 01/2018
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ የፅዳት መጠበቅያ እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች ማለትም ለመንገድ ፅዳት፤ ለቢሮ ፅዳት፤ ለጥበቃና አትክልተኛ፣ ቋሚ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች) ፣ ሌሎች ለውበትና አረንጓዴ ተፋሰስና ለከተማ ግብርና እና ለኪራይ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችና ንብረቶች ፣ የህትመት አገልግሎቶች፣ ልብስ ስፌት፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች፣ የካፍቴሪያ አገልግሎትና የመሣሠሉትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ አካላት፡-
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ የስራ ቀናት በቂርቆሰ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አሰተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የሚገልፅ ክሊራንስ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከዚህ በታች በየሎቱ እንደተዘረዘረው በሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ለሎት 1. 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
ለሎት 2. 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
ለሎት 3. 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
ለሎት 4. 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)
ለሎት 5. 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
ለሎት 6. 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
ለሎት 7. 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
ለሎት 8. 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
ለሎት 9. 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
ለሎት 10, 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
ለሎት 11, 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
ለሎት 12. 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ ውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የሚያቀርቡትን የዕቃ ናሙና ዓይነት ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በጨረታው ሰነድ ላይ በመሙላት በተሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አሥር) ተከታታይ የስራ ቀናት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ለዚህ ስራ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጀናል ዶክሜንትና (ፋይናንሺልና ቴክኒካል) ኮፒ ዶክሜንት ፋይናንሻል ቴክኒካል) አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም፡፡
- ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ዕቃዎች በራሳቸው ወጪ የጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል በማቅረብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ላሸነፉት ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ካቀረቡ በኋላ ለአንድ (1) ዓመት ዋስትና መስጠት አለባቸው፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች በራሳችሁ ያመረታችሁት /እቃ/ ንብረት ካልሆነ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖረባችኋል፡፡
- ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከደምበል የገበያ ማዕከል ጀርባ ወደ ጋዜቦ አደባባይ በሚወስደው መንገድ ደንበል ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር:- 011-5-57-46-77
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
