Tender Detail

Tender Details


የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ. በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአዳማ ከተማ የሚገኘውን የነዳጅ ማደያ ለኦፕሬተር በወኪልነት ለመስጠት ይፈልጋል



የነዳጅ ማደያ ኦፕሬተር ይፈልጋል
         

የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በ አዳማ ከተማ የሚገኘውን የነዳጅ ማደያ ለኦፕሬተር በወኪልነት ለመስጠት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት በቂ ካፒታል፣ የራሳቸው የነዳጅ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ያላቸው እና በማደያ ሥራ በቂ ልምድ  ላላቸው አመልካቾች የጨረታውን ሰነድ ከተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ ዋናው ቢሮ የማይመለስ ብር 250.00/ ሁለት መቶ  ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከነሐሴ  2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ፤ የጨረታውን ሰነድ ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት እንደሚችሉ እና ጨረታውንም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን። ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ በጽሑፍ ወይም በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።

ድርጅቱ የተሻላ የአፈጻጸም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አክሲዮን ማህበር
አድራሻ፡
የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አክሲዮን ማህበር
ቦሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 03/04/05 የቤት ቁጥር 626 ሚኪሊላንድ ጎዳና
ስልክ  011 663 8577/80
011 896 5347/011 869 7264
ፖ.ሣ.ቁ 623 ኮድ1250
ኢሜል ybpetroleum@ethionet.et 
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

Save Tender