ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ዲማ 1፣ ዲማ 2፣ ተርቻ፣ መቱ፣ ነቀምት፣ ጅንካ እና ላሊበላ የዳሽን ቢራ ምርቶችን ለማከፋፈል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
Ref.No: DBSC/PD/ /25
የጨረታ ማስታወቂያ
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ዲማ 1፣ ዲማ 2፣ ተርቻ፣ መቱ፣ ነቀምት፣ ጅንካ እና ላሊበላ የዳሽን ቢራ ምርቶችን ለማከፋፈል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
- በቂ ተሽከርካሪ ማቅረብ የሚችል (የራሱ ቢሆን ይመረጣል)
- ምርቱን ለማከማቸት የሚሆን መጋዘን ያለው (የራሱ ቢሆን ይመረጣል)
- በዘርፉ ተዛማጅ የስራ ልምድ ያለው
- የስራ ማስኬጃ በቂ ካፒታል ያለው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለዚህ የምርት ማከፋፈል የስራ ማስኬጃ ካፒታል ዳሸን ቢራ የሚቆጣጠረው ይሆናል።
- በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ነዋሪ የሆነና በአካባቢው ማህበረሰብ መልካም ስም ያላቸው፤
- ለዋስትና መያዣነተ የሚየገለግሉ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤
- ማህበራዊ እና ህጋዊ ግዴታዎችን በአግባቡ እየተወጣ ያለና ማስረጃ ማቅረ ረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ጨረታው ከመውጣቱ በፊት የስድስት ወር የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ የሚችሉ፤
ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን ሠነድ አሟልተው አዲስ አበባ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ዋና መስሪያ ቤት (22 የቱሪስት ንግድ ስራ ድርጅት አጠገብ) ከሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ገዝቶ በመሙላት ጨረታውን መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው ታህሳስ 01/2018 እስከ ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም ድረስ አየር ላይ የሚቆይ መሆኑን እንገልጻለን∶: ጨረታው ታህሳስ 10/2018 ዓ/ም ከሰዓት 8:00 ተዘግቶ በዚያው ቀን 8:30 ተከፍቶ ቀጣይ ባሉት ተከታታይ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ውጤቱን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን።
ከሠላምታ ጋር
ድርጅቱ
