የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በወንጂ ከረሜላ ፋብሪካ የተመረተ ደስታ ከረሜላ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ ብቃት ያላቸውን አከፋፋዮች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊዎች ጋር ውል በማሰር የተመረተውን ደስታ ከረሜላ በአከፋፋዮች በኩል መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር WSSF/SALES/01/2025
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በወንጂ ከረሜላ ፋብሪካ የተመረተ ደስታ ከረሜላ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ ብቃት ያላቸውን አከፋፋዮች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊዎች ጋር ውል በማሰር የተመረተውን ደስታ ከረሜላ በአከፋፋዮች በኩል መሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
LOT /ምድብ/ |
Description |
|
1 |
የደስታ ከረሜላ አከፋፋዮችን ለመምረጥ የወጣ ግልጽ ጨረታ |
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000473232708 በተጫራቹ ድርጅት ስም ገቢ በማድረግ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ሜክስኮ ፊሲፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 አዲስ አበባ
ለተጨማሪ መረጃ 0115585229/0984550101/0968482445
- ለአከፋፋይነት የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የምርቱን ሂደት ወንጂ ከረሜላ ፋብሪካ በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአከፋፋይነት ሰነድ በአግባቡ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ከመሆኑ በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 201 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚሆን ሲሆን ትክክለኛው የሥራ ቀን የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሠነዱ ውስጥ ይጠቀሳል።
- ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ
