Tender Detail

Tender Details

  • Company Abay Insurance S.C. (ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 154507
  • Websitehttps://abayinsurance.com/
  • Deadline12 Oct 2024, 11:11 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Vehicle

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎

  1. ዓባይ ኢንሹራንስ ኢማ የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እና  ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
  2. ተሸከርካሪዎቹን ፤ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን ለመግዛት በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ለመካፈል የሚፈልጉ ሁሉ ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሠነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በቅድሚያ ከፍሎ ከዋናው መ/ቤት በመግዛት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ከሃናማርያም አደባባይ ወደ ቃሊቲ በሚወስደው ቀለበት መንገድ 800 ሜትር ወረድ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ በመቅረብ ከመስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በስራ ሰዓት‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ ብቻ በመምጣት ማየት ይቻላል።
  3. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ወይም እቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከመስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧቱ 3.00 ሰዓት ድረስ አትላሰ አካባቢ በሚገኘው የአባይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሳጥን ውስጥ የሚጫረቱበትን ዕቃ ኮድ በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ፖስታ ላይ በመጻፍ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ዝቅተኛ ማስያዣ ብር 1,000.00 ሆኖ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን መነሻ ዋጋ 15% በCPO የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ከተከፈተበት ሶስት የስራ ቀናት በኃላ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።
  5.  የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አሸናፊዎች የተሽከርካሪዎችንም ሆነ የዕቃዎችን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል ተሽከርካሪዎችንና እቃዎችን በ10 ቀናት ውስጥ ባይረከቡ ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ - ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ይሰረዛል።
  6. ተሽከርካሪዎች በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ እስከተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር የሻጭ ኃላፊነት ይሆናል:: ተሸከርካሪዎቹ ከተሸጡ በኋላ የሚፈለግ ግብርና ታክስ፣ስም ማዛወርያ እንዲሁም ሌላ ክፍያ ቢኖር የገዢው ኃላፊነት ይሆናል።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀ ቅፅ መሰረት የሚገዙትን ዕቃ ዋጋና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን በግልጽ ሁኔታ በተናጥል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን ኩባንያው ለገዢዎች የሚያስረክበው ገዢዎች በቅድሚያ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚወስነውን ቀረጥና ታክስ ክፍያ ከፍለው ተገቢውን ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ይሆናል።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ተሸከርካሪዎቹንም ሆነ ሌሎች ዕቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ ሳይነጣጥሉ በጠቅላላ በአንድ ጊዜ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ቅዳሜ ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል። ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 0115 - 15 45 07፣ 0115 - 51 08 17 ፣

0115 53 53 00 0913 57 01 55 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ::

Save Tender